Thursday, 29 May 2014

ነገረ ኢትዮጵያ
ግንቦት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 14 2
ርዕሰ አንቀፅ
 እንዲህም ተብሏል!
ነገረ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ ጥር 2006
ዓ.ም ተመሰረተች፡፡ ነገረ-ኢትዮጵያ
በሰማያዊ ፓርቲ አሳታሚነት
የምትታተም ፖለቲካዊ፣ ወቅታዊ፣
ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን
የምትዳስስ በየሳምንቱ አርብ
የምትወጣ ጋዜጣ ናት፡፡
ጋዜጣዋ ሚዛናዊና ነጻ ሆና የማገልገል
መርህ አላት፤ ማንኛውም ሀሳብ በነጻነት
የሚስተናገድባትና የሚንሸራሸርባት
እንድትሆን እንፈልጋለን፡፡ ገዥው
ፓርቲም ቢሆን አቋሙንና ፖሊሲውን
ለመግለጽ ቢፈልግ የሰፊ ሚዲያ ባለቤት
ነው ብለን ዕድሉን አንነፍገውም፤
በራችን ለሁሉም ክፍት ነው፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያ
የአሳታሚ አድራሻ:-
የካ ክ/ከተማ ቀበሌ 09/10 ቤት ቁ.460
E-mail: info@semayawiparty.org
P.O.Box: 180298
ዋና አዘጋጅ ፡- ጌታቸው ሺፈራው
የካ ክ/ከተማ ቀበሌ 01/02
ቤት ቁ. 07/859/14
E-mail:getcholink@gmail.com
ስልክ ቁጥር: 09-10-45-99-32
ምክትል ዋና አዘጋጅ፡- በላይ ማናዬ
የካ ክ/ከተማ ቀበሌ 01/02 ቤት
ቁ.099
E-mail: belaymb@gmail.com
ስልክ ቁጥር: 09-20-19-09-72
አምደኞች ፡-
ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም
ታዴዎስ ታንቱ
ታምራት ታረቀኝ
አፈወርቅ በደዊ
እያስፔድ ተስፋዬ
ሕትመትና ክትትል
 ሳሙኤል አበበ
0913 98 46 40
አታሚ፡- ሰማያዊ ፓርቲ
ሌይ አውት ዲዛይን ፡-
 ደሳለው ጌትነት
ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ዓለም በቴክኖሎጅና በኢ
ኮኖሚው በእጅጉ የተለወጠበት፣ ለሰብአዊ መብትና ዴሞ
ክራሲ መከበር በር የተከፈተበት፣ በሉላዊነት ምክንያት
የዓለም ህዝቦች ከመቼውም ጊዜ በላይ የተሳሰሩበትና ለመ
ተሳሰርም እድል የተገኘበት ጊዜ ነው፡፡ ይህን ነጻነታቸውን
ካገኙ 20 አመት ያልበለጣቸው አገራትም ነጻነታቸውን በአ
ግባቡ ተጠቅመውበት ህዝባቸውን ለመቀየር ችለዋል፡፡ ለአ
ብነት ያህልም ደቡብ አፍሪካን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ከደቡብ
አፍሪካ በተጨማሪ እ.ኤ.አ በ1991 የራሷን አስተዳደር የመ
ሰረተችውና ዓለም እውቅና ያልሰጣት ሶማሊ ላንድ እንኳ
በፍትሃዊ ምርጫ፣ በሰላም መሪዎቿን በመምረጥ በአፍሪካ
ቀንድ ብቸኛዋና በዓለም መንግስታት በአገርነት እውቅና ላገ
ኙትም በምሳሌነት እየተጠቀሰች ትገኛለች፡፡
በሌላ በኩል አገራችን ኢትዮጵያ ረዥም የነጻነትነት
እድሜ ያላት ብትሆንም አሁን ላይ ቀደም ብላ ከቅኝ አገ
ዛዝና ጭቆና ነጻ እንዲወጡ ካገዘቻቸው የአፍሪካ አገራት
ባነሰ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች፡፡ ለዚህ ኋላ ቀርነቷ ደግሞ
ባለፉት 23 አመታት ያገኘቻቸውን አጋጣሚዎች ገዥዎቹ
መጠቀም ባለመቻላቸው እንደዋነኛ ምክንያት የሚጠቀሱ
ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት ስልጣን ላይ የሚገኘው ህወሓት/
ኢህአዴግ መጀመሪያ ላይ የዓለምን ማህበረሰብ ቀልም
ለመሳብ መሰረታዊ ለውጦችን አድርጎ የነበርና እነዚህንም
በህገ መንግስቱ ላይ ያስቀመጠ ቢሆንም ሲተገብራቸው
ግን አልታየም፡፡ በተለይ ስልጣን ከያዘ ከአራትና አምስት
አመት በኋላ ወደ ነበረበት ‹‹ግራ ዘመምነት›› በመመለስ
በህገ መንግስቱ የፈቀዳቸውን መብቶች እንደገና በግልጽ
ሲደፈጥጥ ተስተውሏል፡፡
ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን እንደያዘ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ
የህትመት ሚዲያዎች ፈቃድ አግኝተው ለህዝብ መረጃ
በማድረስ ላይ የነበሩ ቢሆንም ሚዲያ ህዝብን ማንቃቱን
ያልወደደው ገዥው ፓርቲ እየቆየ አፈናውን ተያይዞታል፡፡
በመሆኑም በርካታ ሚዲያዎች ወደ አደባባዩ ወጥተው እን
ደገና ለመዘጋት ተዳርገዋል፡፡ ጋዜጠኞች ታስረዋል፤ እየታ
ሰሩም ነው፡፡ በጫናው ምክንያት ተሰደዋል፤ እየተሰደዱም
ይገኛሉ፡፡ በተለይ ህወሓት/ኢህአዴግ የደነገጠበት የ1997
ምርጫን ተከትሎ በርካታ የህትመት ሚዲያዎች ሲዘጉ፣
ጋዜጠኞች በአገር ክህደት ወንጀል ተከሰው ዘብጥያ ወርደ
ዋል፡፡ በርካቶቹ ተሰደዋል፡፡ ይህን ሁሉ ጫና ችለው ለህ
ዝባቸው መረጃ ለማድረስ የጣሩት እንደ እስክንድር ነጋ፣
ርዕዮት ዓለሙና ውብሸት ታየ ያሉት ደግሞ በአሁኑ
ወቅት ‹‹አሸባሪ›› ተብለው እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
በቅርቡ ከዞን ዘጠኝ አባላት ጋር የታሰሩት ሶስት ጋዜጠኞች
ስርዓቱ ባለፈው 23 አመት ያደበረውን የአፈና ባህል አጠ
ናክሮ እንደቀጠለ የሚያሳይ ሆኗል፡፡
በተመሳሳይ የመደራጀት፣ የመሰብሰብና ሌሎች መብቶች
ባለፈው 23 አመት ህገ መንግስቱ ላይ ከሰፈረው በተቃራኒ
እየተደፈጠጡ ቀጥለዋል፡፡ በአንድ ወቅት ጠንካራ ተቃዋሚ
እንዳጣ በግልጽ ሲናገር የነበረው ገዥው ፓርቲ ከ1997
በኋላ ለተቃዋሚዎች መፈናፈኛ ላለመስጠት በርካታ ፀረ
ህገ መንግስታዊና አፋኝ አዋጆችን አጽድቆ በህግ መሳሪያ
ነት እየገዛ ቀጥሏል፡፡ ባለፉት 8 አመታት ህገ መንግስቱ የፈ
ቀደው ሰላማዊ ሰልፍ በገዥው ፓርቲ ተከልክሎ ቆይቷል፡
፡ በአሁኑ ወቅትም በተቃዋሚዎች ግፊት የተጀመሩ የተቃ
ውሞ ሰልፎች በገዥው ፓርቲ የደህንነትና የፖሊስ ኃይል
የሚጠበቅባቸውን ያህል ሚና እንዳይወጡ ተከልክለዋል፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎች ህጋዊ በሆነ መንገድ የስብሰባ አዳራ
ሽና ሌሎቹንም ለትግሉ ሊያገኙዋቸው የሚገቡ አገልግሎ
ቶችን እንዳያገኙ ገዥው ፓርቲ ጠንክሮ እየሰራ ይገኛል፡፡
ይህም የፖለቲካ ኃይሎች በሰላማዊ ትግሉ ተስፋ እንዲቆ
ርጡና ሌሎች ሰላማዊ ያልሆኑ አማራጮችን እንዲከተሉ
እስከማድረግ ደርሷል፡፡ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በተጨማሪ
ሲቪክ ማህበራትና ሌሎችም ለህዝብ ጥቅም የሚቆሙ የህ
ዝብና የመንግስትን ተቋማት አንድም ለራሱ መጠቀሚያ
ማድረጉ ከዚህም በተጨማሪ ስራቸውን እንዳይተገብሩ መሰ
ናክል መፍጠሩ ህዝብ ድምጹን የሚያሰማበት መድረክ እን
ዲያጣ ተደርጓል፡፡
ሚዲያ፣ ተቃዋሚዎችና ተቋማት በመዳከማቸው ገዥው
ፓርቲና ፖለቲከኞቹ ያለምንም ተጠያቂነት የአገሪቱን
ሀብት ተጠቅመውበታል፡፡ በመሆኑም ባለፉት 23 አመታት
ከአገርና ከህዝብ ጥቅም ይልቅ ግለሰባዊ፣ የፓርቲና ቤተሰ
ባዊ ጥቅምን ማጋበስ የስርዓቱ ባህሪ እንደሆነ ታይቷል፡፡
በዚህም ምክንያት ህዝብ ከአገሩ ኢኮኖሚ የሚገባውን እን
ዳያገኝ ተደርጓል፡፡ በሙስና፣ በስርዓቱ ደጋፊነትና በመሳሰ
ሉት ካልሆነ ህጋዊ መንገድን የያዘ ዜጋ ስራ መስራት ባለ
መቻሉ አገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እን
ዳታገኝ ተደርጋለች፡፡ ምሩቃን፣ ከስርዓቱ ጋር ግንኙነት የሌ
ላቸው ምሁራንና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ህጋዊ
በሆነው መንገድ ጥቅም ባለማግኘታቸው ለስደት፣ ለድህ
ነት ተዳርገዋል፡፡
በተቃራኒው ግን ይህ ያፈጠጠ እውነታ ተገልብጦ የግንቦት
20 ፍሬዎች እየተባለ ህዝብ ባዶ ፕሮፖጋንዳ ይጋታል፡
፡ በመሆኑም ገዥው ፓርቲ እንደሚለው ግንቦት 20 የኢ
ትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱን ያገኘበት ሳይሆን ከአንዱ አምባገነን
ስርዓት ወደ ሌላ መልኩን የቀየረ አምባገነን ስርዓት የተሸ
ጋገርንበት መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ እናም ያለን
በትን ትክክለኛ መልክ ሸፋፍኖ ስለሌለ ለውጥ ህዝብን በፕ
ሮፖጋንዳ ከማደንቆር ይልቅ ወደ ትክክለኛ የህዝብ ተጠቃ
ሚነትና ነጻነት የሚያደርሰውን መንገድ ይዞ ለአዲስ ለውጥ
መስራት እንደሚገባ መገንዘብ ይገባል

No comments:

Post a Comment