Thursday, 29 May 2014

ግንቦት 20 የኢትዮጵያ ውርደት ጥቁር ቀን


    May 28, 2014
ከሮበሌ አባቢያ
በአምቦ ከተማና በሌሎች የኦሮምያ ክልል ውስጥ የዩኒቭርሲቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ያቀረቡት ሕገ-መንግሥታዊ ጥያቄ ያገኘው ምላሽ በጨካኙ የአግዓዚ ጦር አልሞ ተኳሾች በጥይት መደብደብን ስለሆነ፣ ይህንን አሰቃቂ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ ያውም ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰብአዊ መብት መከበር ግምባር ቀደም መመሪያ ሆኖ በዓለማችን ላይ በገነነበት ጊዜ በመፈፀሙ፣ ወንጀለኞች ከተጠያቂነት ሊያመልጡ አይችሉም። ይህንን የተገነዘበው የባእዳንን ዓላማዎች ለማስፈፀም በጫንቃችን ላይ የተኮፈሰው የወያኔ መንግሥት አገልጋዮቹ ለፈፀሙት ኢሰብዓዊ ጭፍጨፋ ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ ወንጀሉን በመሸፋፈን የሕዝብ ትኩረት ወደ እርሱ ሙገሳ እንዲዞር እነሆ 23ኛውን የወረራ በዓሉን ሲያከብር በመፍጨርጨር ላይ ይገኛል። ነገር ግን ግንቦት 20 የኢትዮጵያ ውርደት ጥቁር ቀን ተብሎ መዘከሩ አይቀርም።Ginbot 20 TPLF/EPRDF's holiday
ወያኔና ከርሱ በፊት የነበሩት ሁለት መንግሥታት
ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ጀምሮ ጥቂት ምሳሌዎቸን ጠቅሼ በማወዳደር የወያኔን ውሸት ላንባብያን ላቅርብ፦
1. የ1997 ምርጫ አለደም መፋሰስ የሥልጣን ሽግግር የተደረገበት ታሪካዊ ወቅት ነው ሲል ነውረኛው የወያኔው አምባገነን መሪ መለስ ዚናዊ ሲመፃደቅ በኢትዮጵያ ቴሌቪዠን ታይቷል። ያ አልበቃ ብሎት፣ ወያኔ በ99.6% አሸንፌያለሁ ብሎ የቀጠፈበት የ2002ቱ ደግሞ በጥራቱ እንከን ያልተገኘበት ምርጫ ነበር እያለ መለስ ዚናዊ ሲያፌዝብን አዳምጠናል። በእነዚህ ሁለት ምርጫዎች፦ የሕዝብ ደምና ሕይዎት ተሰውቷል፣ የመራጮች ድምፅ ተሰርቋል፣ ድላቸው ተቀምቷል፣ አሸናፊዎች ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ተወርውረዋል፣ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ በተለይ ወጣቶች የምርጫውን መጭበርበር በአደባባይ ስለተቃወሙ በግፍ ታስረዋል። ይህንን አረመኔያዊ የወያኔ ፋሺስታዊ ተግባር፣ ታሪክ ምንጊዜም አይረሳውም።
2. የብሔር ብሔረሰቦች ጉዳይ ሲነሳ አፄ ኃይለ ሥላሴ በድል አድራጊነት ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱ ሕዝባቸው በቆየው እምነቱ፣ ባሕሉና ልማዱ መሠረት መብቱ እንዲጠበቅለት ወዲያው አውጀዋል። በዘመነ መንግሥታቸው የባህል ሚዩዚየም እንዲከፈት አድርገዋል። አፄው ባመቻቹላው አዋጅ መሠረት፦ ሀ) በአዲሰ አበባ ጊፍቲ (እመቤት) ጂፋሬ የተባሉት ባለውቃቢ የጥንቆላ አገልግሎት ይሰጡ ነበር፤ አልተባበርህም ያሉትን አርበኛ አባታቸውን ፋሺስት ኢጣልያ ቁልቆል ዘቅዝቆ በመግደሉ ይህ እንደ ውለታ ተቆጥሮ፣ ወ/ሮ ጂፋሬ “የኢትዮጵያ ሀገር ፍቅር ማህበር” ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል፤ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ፣ ልዑል አልጋወራሽ አስፋወሰን በቀብር ሥነሥርዓታቸው ላይ መገኘታቸውን አውቀለሁ፤ ለ) አምቦ ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ ደንፋ እየተባሉ የሚጠሩ በንጉሠ ነገሥቱ የሚታወቁ ባለውቃቢ እንደነበሩ አውቃለሁ፤ አፄው አዘውትረው አምቦን ይጎበኙ ስለነበር፣ ደንፋ ፈረሰኞች እስከ ጊንጪ(36 ኪሎሜትር ከአምቦ) ድረስ ልከው እንደሚያሳጅቧቸው ይታወቃል፤ ሐ) ሕዝብ ታዋቂ የማምለኪያ ቦታዎች፣ የየረሩ ንጉሥ ተብሎ የሚጠራው ባለውቃቢ የሚኖርበት በአዲሰ አበባ አካባቢ፣ ሆራ አርስዴ በቢሾፍቱ፣ የአርሲ እመቤት መኖሪያ በአርሲ፣ ሶፍ ዑመር በባሌ እንደነበሩ ይታወቃል።
3. የአዲስ አበባ ነዋሪዎችና ዛሬ መሬቱ የሚነጠቀው የኦሮም ተወላጅ አያት/ቅድመ አያት የአካባቢወ ሕዝብ ማንም ለፖለቲካ መጠቀሚያነት ሳያዘው ለጥምቀት በዓል ወደ ጃንሜዳ እየጎረፈ እጅግ የሚማርኩ የየባህሉን ዘፈኖች፣ ጭፈራዎችና ውዝዋዜዎች መመልከት ለኢተዮጵያን ኩራትና ፈንጠዝያ፣ እስከ ዛሬም ለቱሪስቶች መስህብ ሆኖ በመገኘቱ የወያኔ መሪዎች ዶላር ያፍሱበታል። በሕግ የተደነገገ የአለባበስ ኮድ ስላለነበረ ሁሉም በየባህሉ ልብስ አጊጦ ጃንሜዳን አጥለቅልቆ ያውባት ነበር። በወያኔ አበረታችነት ሳይሆን እስካሁንም እንደዚያው ነው።
4. በደርግ ዘመነ መንግሥት የብሔር ብሔረሰቦች ኢንስቲቱት ተቋቁሞ ነበር። “የዘር የሃይማኖት ልዩነት አንሻም፣ ይላሉ ልጆችሽ ኢትዮጵያችን ትቅደም”፣ ተብሎም ተዘምሯል። የባህል ዘፈኖችና ቲያተሮች በየክፍላተ ሀገር አብበው ነበር።
5. የወያኔ ዘመነ መንግሥት እስር ቤቱ በኦረሚፋ ተናጋሪዎች ታጭቋል ተብሎ ተነግሮለታል… የብሔር ብሔረሰቦች ወያኔ ለፖለቲካ ፍጆታ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የማሞኛ በዓል ከመሆን አልፎ፣ የ83ቱንም ብሔር ብሔረሰቦች ቋንቋዎችንና ልማዶች አቆይቶ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ የሚዘልቅ አይደለም።
6. ረሀብን በማስወገድ ረገድ ሶስቱም መንግሥታት ሀላፊነታቸውን ሙሉ በሙሉ አልተወጡትም። የአፄው አገዛዝ የወሎውን ረሀብ ለመሸሸግ መሞከሩ ሊወገዝ ይገባዋል። የደርግ መንግሥት ረሀብ በሀገሪቱ ውስጥ እያለ ሥልጣን ላየ የወጣበትን 10 ዓመት ለማክበር የአልኮል መጠጦችን ከውጪ ሀገር በዶላር ማስገዛቱ ያስወግዘዋል። ወያኔ የሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት አሰመስግቤያለሁ እያለ ሲፎልልባት በቆየበት ሀገር 6.5 ሚሊዎን ረሀብተኞች ኸተባበሩት መንግሥታት የምግብ እረዳታ ይጠብቃሉ መባሉ የአገዛዙን ጭካኔ ያመለክታል።
7. የወያኔ መንግሥት መሪዎች ለሱዳን መሬት ቆርሰው ለመስጠት እየተሯሯጡ ነው። የቀድሞ መንግሥታት እንኳን ሊያደርጉት የማያስቡት ወራዳ ድርጊት በታሪክ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል
8. ወያኔ ኢትዮጵያን አስገንጥሎ ወደብ-አልባ ያደረጋት ሞራላዊም ሆነ ሕጋዊ ብቃት የሌለው ቅጥረኛ መንግሥት።
9. መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶችን ረገጣ በተመለከተ የወያኔ መንግሥት ሬኮርድ አሳፋሪና ዘግናኝ መሆኑን ዓለም ያወቀው ሐቅ ነው። እነዚህን መብቶች ለማስከበር የወያኔን አገዛዝ በተባበረ ተቃውሞ ማንበርከክ ግድ ይላል።
10. በአፄው ዘመነ መንግሥት በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመሥራት ጥናቱ ተጠናቆ ነበር፤ ሆኖም በገንዘብ እጦት ምክንያት ግድቡ አልተሰራም። የግብፅ ኤክስፐርቶችም በአባይ ወንዝ ላይ እስከ 40 ግደቦች ለመሥራት እነደሚቻል በጠናት አረጋግጠው፣ ችግሩ የገንዘብ ጉዳይ መሆኑን አስምረውበታል። የህዳሴው ግድብ የሌሎችን የልማት ፕሮጄክቶች በጀት የሚሻማ የመዝረፊያ ፕሮጀክት ከመሆኑም በላይ፣ በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል የሦስትኦሽ ወገን ውይይት ተደርጎ ስምምነት ካልተደረሰ በስተቀር፣ ውጤቱ ንትርክና አልፎም ወጣቱን ትውልድ በማያባራ ጦርነት ውስጥ መዝፈቅ ይሆናል። የአባይ ውሀ የገዘፈው ከአማራውና ከኦሮሚያ ክልሎች በሚያፈሱለት ገባር ወንዞች አማካይነት ነው። ታዲያ ሁለቱ ክልሎች ከህዳሴው ግድብ የሚያገኙት ድረሻቸው ምን ያህል ነው? የብሔር ብሔረሰቦችን ከፋፋይ ፖሊሲ በውስጥ እያዳከመን እያለ ሁኔታውን በሚያባብስ ተግባር ላይ ማተኮር የሚያስከትለው አደጋ ከባድ ስለሚሆን በቀና መንፈስ መወያየት ለሁሉም ይበጃል።
አለመታመን፣ ለወያኔ ሰቀቀን
ዋሽቶ ማስዋሸት የወያኔ ቁንጮዎች የፖለቲካ መሳሪያ ሆኖ ቆይቷል። ሆኖም ዛሬ፣ ውሸት አገዛዙን የሕዘብ ተዓማኒነት አሳጥቶት ውድ ዋጋ እያስከፈለው ይገኛል። ጉዳቱ ለምንወዳት ሀገራችንም ጭምር ነው። ምክንያቱም የውጭ ጠላት መጥቶባት ክተት ቢታወጅ፣ የተለመደ ውሸቱ ነው በማለት ወያኔን የሚያምን ኢትዮጵያዊ ስለማይገኝ በቆየው ባህላችን መሠረት ሆ! ብሎ የሚነሳና አጥቂውን ለመፋለም ፈቃደኛ ተዋጊ እንደማይገኝ አምናለሁ።
በደርግ ዘመነ መንግሥት ማብቂያም ውሸት ስለበዛ፣ የአካባቢ ወጣቶች እንደተለመደው በአርበኝነት ወኔ ተነሳስተው የክተት ጥሪ ለመቀበል ፈቃደኞች ሁነው ስላልተገኙ፣ በቀበሌዎችና በገበሬ ማህበራት አስገዳጅነት እየታፈሱ ለለብ ለብ ሥልጠና ወደ ወታደራዊ ተቋማት ከተላኩ በሗላ በውጊያ ልምድ ያዳበረውንና በአረቦች ፔትሮ-ዶላር ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታቀውን የወያኔ ሠራዊት እንዲገጥሙ የተገደዱትንና የረገፉተን ወጣቶች ማሰታወስ ግድ ይላል። አስከፊው ሁኔታ እዚያ ደረጃ ላይ እሰኪደርስ ድረስ ደርግ ወያኔን እንደ ተራ ሺፍታ እያቃለለ ፕሮፓጋንዳውን ይነዛ ነበር። የሥልጣን ባለቤት የሆነውን ሕዝብ መዋሸት፣ የሚያስከትለው መዘዝ ብዙ ነው።
ከእንግሊዞች ፖለቲካ ምን ይማሯል?
ፀሐይ በእንግሊዝ ግዛት ከቶም አትጠልቅም (The sun never sets on the British Empire”) ተብሎ ሲጠቀስ ከልጅነቴ ጀምሮ እሰማ ነበር። የጥቅሱም ትርጉም፣ እንግሊዝ (ብሪቲሽ) የቅኝ ግዛቶቿን ጨምሮ በዓለማችን ላይ የነበራት ግዛት እጅግ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ፣ ጀምበር አንዱ ጋ ስትጠልቅ ሊላው ጋ ትወጣለች ማለት ነው። ዛሬ ደሞ፣ ጀምበር በእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገሮች ላይ አትጠልቅም ለማለት እደፍራለሁ። አዎ! በያዝነው 21ኛው ክፍለ ዘመን ብዙ ቋንቋዎች እየከሰሙ በእንግሊዝኛ ቋንቋ እንደሚተኩ አዝማሚያው በሂደት እየታየ ነው። አንዳንድ ጥናቶች ይህንኑ አዘማሚያ እያሳዩ ነው። የቋንቋዎች ብዛት እያነሰ በሄደ ቁጥር፣ የሰው ልጆች የርስ በርስ መግባባት እየጨመረ እንደሚሄድ የሚያጠራጥር አይመስለኝም።
እንግሊዞች ፖለቲካቸው የሚሳካላቸው በእራሳቸው ላይ መሳቅ ስለሚችሉ ነው ተብሎ ሲነገርም ሰምቻለሁ። በአሁኑ ጊዜ በአውሮፓ ህብረት ውሰጥ እንቆይ በሚሉት በሌበር ፓርቲ እና ሊብራል ፓርቲ ባንድ ወገን፣ እና የለም ከህብረቱ እንውጣ በሚለው የወግ አጥባቂው ፓርቲ መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ እንደሚሄድ የተገነዘቡት ሌሎች አውሮፓውያን፣ እንግሊዝ የሌለችበት ፖለቲካ አይጠፍጥም እያሉ ሲተቹ ይሰማሉ፡፤
በኢትዮጵያ ሀገራችንም ቢሆን አማራና ኦሮሞ የማይሳተፉበት የጋራ ፖለቲካ ከሌለ፣ ኢትዮጵያ እንደ ውሁድ ሀገር አትኖርም፤ የአፍሪካ ሕብረትም ሕልውና አጠራጣሪ ይሆናል። ታዲያ የጥቁሮቹ የኩሽ፣ የካምና የሴም ልጆች እጣ ፋንታ ምን ሊሆን ነው? አዎ! የዛሬን ስናነሳ ትናንትን ሳንረሳ አስታውሰን በሞኝነታቸን ላይ ስቀን ስህተታችንን አርመን ወደፊት መጓዝ ብልህነት ነው።
በሀገራችን በኢትዮጵያም ቢሆን የቋንቋዎች ብዛት እያነሰ መሄዱ አይቀሬ መሆኑን ካሁኑ አምኖ መቀበል ብልህነትና አርቆ አስተዋይነት ነው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም። በዚህ አስተሳሰብ በመጓዝ፣ ወያኔ ከጫነብን ደም አፋሳሽ የጎሳ ፖለቲካም ለመገላገል ፍቱን መድሐኒት አአአእናገኛለን።
የግል ሚዲያ/ነፃ ፕሬስ መታፈንና መዘዙ
በእድሜዬ ዘመን ያጋጠሙኝን ሶስት መንግሥታት ላንሳ። እነዚህም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ የመንግሥቱ ኃይለማርያም (ደርግ) እና እንደወራሪው ፋሺስት ጣልያን ኢትዮጵያውያንን በጥይት የሚቆላው ወያኔ ናቸው። ሦስቱም የነፃ ፕሬስና መሠረታዊ የሕዝብ መብቶች በተለያየ ደረጃም ቢሆን አንቀው በመያዛቸው ይታወቀሉ። በዚህ ምክንያት ሁለቱ ከሥልጣናቸው ተዋርደው ሊወድቁ በቅተዋል፤ ወያኔም ተመሳሳይ ዕጣ ይጠብቀዋል። ተንሽ ላብራራ፦
1. ጃንሆይ ያፈኑትን የፕሬስ ነጻነት ደርግም ወርሶ በሥራ ላይ ስላዋለው፣ በመንግሥት ሙሉ ቁጥጥር ሥር በሚገኙ ሚዲያዎች ለሚነዛባቸው የሃሰት ፕሮፓጋንዳና የስም ማጥፋት ዘመቻ ዓፄውም ሆኑ ደጋፊዎቻቸው በነፃ ፕሬስ አማካይነት አጸፋዊ መልስ ለመስጠትና እራሳቸውን ለመከላከል አልቻሉም። ለምሳሌ ገና ወጣት ሳሉ በደጃዝማችነት ማዕረግ የአስበ ተፈሪ አውራጃ ገዢ ሆነው የከተማውን መሬት ሸንሽነው አላንዳች አድልዎ በርስትነት ማከፋፈላቸው፣ በ1946 ዓ.ም በፕሬዚዳንት አይዘንሐወር ጋባዥነት ከአሜሪካ ጉብኝት በሗላ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ፣ ሕዝቡ ታጥቆ በመነሳት በርሻ ልማት እንዲሰማራ ለማረስ ለሚፈልግ አትዮጵያዊ በነብስ ወከፍ አንዳንድ ጋሻ የገጠር መሬት እንዲሰጥ አውጀው እንደ ነበርና በዚህ አዋጅ የሰፈሬ ሲቪሎች ተጠቃሚ እነደበሩ አውቃለሁ፣ከኔ ጭምር በርካታ የአየር ሀይል መኮንኖች በሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ነጭ ሳር ተብሎ በሚጠራው ቦታ የተሰጠንን አንዳንድ መሬት ለማልማት በዝግጅት ላይ ነበርን። ጃንሆይ ሌሎች አያሌ አኩሪ ሥራዎችን ማከናወናቸው ሐቅ ነው፡፡ ነፃ ፕሬስ ቢፈቀድና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተፈጥረው ቢሆን ኖሮ እነዚህን አኩሪ ክንውኖችን በመጥቀስ ደጋፊዎቻቸው ሊከራከሩላቸው በቻሉ ነበር፡፡ ግና፣ የአምባገነን ትዕቢታቸው ስላልፈቀደላቸው ነፃ ፕሬስ መፍቀድ አልተዋጠላቸውም። ሰለዚህ ተዋርድው ከዙፋናቸው ወረዱ፤ የሌሎችም ዲክታተሮችም ዕጣ ፋንታ ከዚህ የተለየ እንደማይሆን ታሪከ አስተምሮናልና።
ብዙዎቻችን አጥብቀን የታገልንለት የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ንጉሠ ነገሥቱ በሕይዎታቸው እያሉ አቆጥቁጦ እያደገ ከእርሳቸው ሕልፈት በሗላ የእንግሊዞችን ሞዴል የመሰለ ሞናርኪ ሊፈጠር በቻለ ነበር። እኔም የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት እንዲፈጠር ሁኔታ እንዲመቻችና ነፃ ፕሬስ እንዲፈቀድ ያቀረብኩት ተማጽኖ በኢትዮጵያን ሄራልድ ላይ በ1966 ዓ.ም ታትሞ ነበር። ግን ሰሚ አላገኘም፤ ለዚያውም በዚያን ጊዜ ማን ተደማምጦ።
2. የደርጉ ሊቀ መንበር ሻለቃ መንግስቱ ኃይለማርያም ነሐሴ 12 ቀን 1966 ዓ.ም በቁጥር አ/ኮ/072/66 ለሁሉም ወታደራዊ ክፍሎችና በየጠ/ግዛቱ ለተቋቋሙት ንዑስ ኮሚቴዎች በያሉበት ከጻፈው ደብዳቤ ጋር አያይዞ ሀያ (20) ነጥቦችን የያዘ አንድ ገጽ የሥራ ዝርዝር መመሪያ ልኮ ነበር።
የአየር ኃይል ንዑስ ደርግ ከመመሪያው ውስጥ የተወሰኑትን መርጦ በተለይ በተራ ቁጥር 15 የተገለጸውን ቅድሚያ በመስጠት ነሐሴ 17 ቀን 1966 ዓ.ም. ቁጥር ፦ አሀ/ንደ/ // /66 በጻፈው ደብዳቤ የሚከተለውን መልስ ሰጥቷል፦
“ጉዳዩ፦ በአየር ኃይል ንዑስ ደርግ የቀረበ ሀሳብ
ለጦር ሀይሎች፣ ለፖሊስ ሠራዊትና ለብሔራዊ ጦር አጠቃላይ ደርግ
የአየር ሀይል ንዑስ ደርግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እንዲፈጸሙለት በአየር ሀይል ሠራዊት ስም ይጠይቃል፦
የተጀመረው ንቅናቄ “ብሔራዊ” እንዲሆን የሰላማዊ ሕዝብ ተካፋይ መሆን አለበት። ስለዚህ ለምሳሌ፦
ሀ. ከኢትዮጵያ ሠራተኞች አንድነት ማህበር፣
ለ. ከአሠሪዎች ማህበር፣
ሐ. ከዩኒቨርስቲ መምህራን፣
መ. ከዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣
ሠ. ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር፣
ረ. ከብሔራዊ ሸንጎ /ፓርላማ/
ሰ. በቻርተር ከሚተዳደሩ መሥሪያ ቤቶች፣
ሸ. ደርጉ ከሚያምንባቸው ልዩ ልዩ ሌሎች ክፍሎች መወከል አለባቸው።”
ቀን የደረስንበትን ውሳኔ ልዕልቲቱ ማታ ታሽረዋለች እያሉ ጠቅላይ ምኒስትሩ ያማርራሉ ተብሎ ስለተወራ፣ የታሠሩት ባለሥልጣኖች የቴሌቪዠን ሰዓት ተሰጥቷቸው አመራር ለመስጠት የተቸገሩበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንዲገልፁ ይደረግ ዘንድ በሻለቃ አዲስ ተድላ በኩል በጽሑፍ የቀረበው ሀሳብ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ከባድ ስህተት ሊፈፀም ችሏል። ምክር አልሰማም ባይነቱ የደርግን መንግሥት አንኮታኮተው!
3. ነፃ ፕሬስ፦ በሰው ልጆች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሕይዎት ውስጥ ወሳኝ ሚና አለው። ነፃ ፕሬስ የዜጎች እኩልነት መለኪያ ነው፤ የግለሰብ ነፃነት ዋስትና ነው፤ የሥልጣኔ ምልክት ነው፤ የሕዘብን ብሶት መግለጫ ነው፤ የመልካም አስተዳደር መንገድ ጠቋሚ ነው። እነዚህን ለመረዳት ያልፈለገው የወያኔ አገዛዝ ገና ሥልጣን እንደያዘ ማበብ ጀምረው የነበሩትን ድንቅ ጽሑፎች አከሰመ፤ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት አውታሮች በሙሉ በአገዛዙ ጥብቅ ቁጥጥር ስር ዋሉ። ስለዚህ ከሕዝብ ተለይቷልና የሕወሐትም ሞት አይቀሬ ነው!
ወያኔና ሙስና
የወያኔ ቁንጮ መሪዎችና ቡችሎቻችው ከማይወጡበት የሙስና ባህር ውስጥ ገብተው በመስጠም ላይ ናቸው።
ኢኮኖሚያቸው በአሁኑ ጊዜ እየመጠቀ በመሄድ ላይ የሚገኘው የቻይና ኮሙኖስት ፓርቲ መሪዎች፣ በሀገራቸው ስር የሰደደ ሙስና የቱን ያህል እንዳሳሰባቸው ለመግለፅ እነዲህ ብለው ነበር፦
“ይህንን ጉዳይ ቆጣጠር ካቃተን፣ ፓርቲውን ለሞት ከሚዳርግ አልፎም ከሚገድል፣ ሀገሪቱንም ለውድቀት የሚያበቃ ሁኔታ ሊመጣ ይችላል (“If we fail to handle this issue well, it could prove fatal to the Party, and even cause the collapse of the Party and the fall of the state”. ) ብለው የፓርቲው ዋና ጸሐፊ የተነገሩትን እንደ አውሮፓ ኖቬምበር 15 ቀን 2012 “Reform in China vs crisis within EPRDF” በሚል ርዕስ ከተብኩትን ጽሑፍ በድረ-ገጾች ላይ አስለጥፌ አስነብቤያለሁ።
ቅጥረኛው የወያኔ ነውረኛ አገዛዝ ላለፉት 23 ኣመታት የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅሞች ሲያዳሽቅ፣ ንብረቷን ሲመዘብርና ንዋይና የቡና ምርት የመሳሰሉትን ሀብት ሠርቆ ወደ ውጪ ሀገር በስውር በማሸጋገር ከብሮና ብቸኛው ባለመሬት ሆኖ፣ የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ የበላይነትን አስፍኖ፣ የዴሞክራሲ ግብዓቶቸን በሙሉ ተቆጣጥሮ እነሆ ዛሬ በማንአለብኝነት ሙስና አለቅጥ ባልጎ እንዳሻው እየገደለ፣ እያሰረ፣ ዜጎችን ከመኖሪያቸው እያፈናቀለ፣ ይገኛል። የወያኔ ቁንጮ መሪዎችና ቡችሎቻችው ከማይወጡበት የሙስና ባህር ውስጥ ገብተው በመስጠም ላይ ናቸው።
ይህ መውደቂያው አይቀሬ፣ ከአንድ አናሳ ጎሳ ከተውጣጡ በዘረፋ የከበሩ ጄኔራሎች የሚደገፈው መንግሥት እስከ አሁን ካደረሰው ዘግናኝ በደል በላይ ሌላ ሳጨምር በአፋጣኝ በቃህ ሊባል ይገባል!!!
ስለ የሙስና ንግሥት ሕዝቡ ምን ይላል?
ወልቃይት ብናስጠይቅ አሉን እዚያ የለች
ቀዳማዊ እመቤት ታዲያ ወዴት ሄደች
የሙስና ንግሥት ዘርፋን የከበረች
ፈልጓት ባካችሁ የት እንደ ደረሰች
እንድንፋረዳት ፍርድ ቤት አቅርበን
መች እንዲህ እንቀራለን ተገድለን ተገርፈን
ባባታችን ሀገር ተዘርፈን ተዋርደን
የመብት ጥያቄ ስናነሳ ታስረን
መለስ የዘራውን የጎጠኞች ፍሬ
አድጎ ሳይስቸግር እንቅጨው በጥሬ
ማምከን በተግባር ነው አይደለም በወሬ
ይህ ነው የኔ ምኞት ለኢትዮጵያ ሀገሬ
ንግሥቲቱን አየን ጥቀር ለብሳ ከስማ
በጣይቱ ከተማ ተደብቃ ከርማ
ወንጀሏ ይዘርዘር አንዱ ይንገር ላልሰማ
ወህኒ ቤት እንስደድ አዜብ ጎላንማ
ኑሮን ያልጠገቡ የኦሮሞ ልጆች ወጣት ተማሪዎች
ሕይዎታቸው ጠፍቶ፤ ደማቸው ተረጭቶ ባጋዚ ተኳሾች
አርፋ አትቀመጥም ሕዝብን ካለጋጨች፤ ካላተራመሰች
ታዲያ እንዴት ይኖራል አዜብ ተጠፍራ ቶሎ ካልታሰረች
ጸሎቴና አድናቆቴ
በ24/5/2014 መድረክ አዲስ አበባ ላይ ባካሄደው ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የታየው የተቃዋሚ ሀይሎች አስደናቂ ትብብር የበለጠ አይሎ፣ ጎልብቶ፣ አድጎና ፈርጥሞ ወያኔን በሰላማዊ መንገድ ለማንበርከክና በእናት ሀገራችን ውስጥ ጎጠኝነት ፈጽሞ እንዲከስም የዘወትር ጸሎቴ ነው።
ኦቦ ቡልቻ ደመቅሳ ላሳዩት ሞራል ገንቢ ተሳትፎ አድናቆቴን ከልብ እገልጻለሁ፤ ለመድረክ አመራሮችና አባላት ልባዊ መሥጋናዬን አቀርባለሁ።
የታሰሩት የፖለቲካና የህሊና እስረኞች አለምንም ቅድመ-ሁኔታ በአስቸኳይ ይፈቱ!
በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ወንጀል የፈፀሙ ሁሉ ለፍርድ የቅረቡ፤ ለሞቱት ተማሪዎች ቢተሰቦች መንግሥት ካሳ ይክፈል!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
rababya@gmail.com

ቅድመ ምርጫ አፈናው በውይይት እንዲተካ እንጠይቃለን!! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

May 28, 2014

እንደሚታወቀው የግንቦት 2ዐን 23ኛ ዓመት ለማክበር ጉድ ጉድ እያለ የሚገኘው ገዥ ፓርቲ ወደ ጠቅላይ አምባገነን ፓርቲነት ከተለወጠ ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በ1983 ዓ.ም ሀገሪቱን ከመቆጣጠራቸው በፊት በርካቶች ስለ ነፃነት፣ እኩልነት፣ ሰብአዊ መብት መከበርና ዴሞክራሲ ሥርዓት መስፈን ክቡር ህይወታቸውን እንዲገብሩ ተደርጎ በተገኘ የዜጎቻችን መስዋእትነት መንበረ ሥልጣኑን ቢጨብጡም በተግባር ዋጋ የተከፈለበትን ዓላማ ለማሳካት አልቻሉም፡፡ እንዲሁም የህዝቦችን ነፃነት በጉልበት በመቀማት፣ ሰብአዊ መብትን በመጋፋት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱን ለማስመሰያነት በንድፈ ሃሳብ አስፍረው በተግባር በዜጎችዋ ግፍ በመፈፀም ነፃነውን ፕሬስ እንደጠላት በማየት፣ ተቀናቃኝ ኃይሎችንና የፖለቲካ መሪዎችን በማሰርና በማፈን፤ በነፃነት የመደራጀት መብትን በመጨፍለቅ በአጠቃላይ ፍፁም አምባገነን የሆነ ስርዓት በመዘርጋት ላይ ነው፡፡UDJ/Andinet party logo
ሥርዓቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የመሻሻልና የሁነቶች የመማሪያ ባህሪ ሊኖረው አልቻለም፡፡ ይልቁንም ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ መስመር ውጭ የሆኑትን በጅምላ በመፈረጅና በተናጠል ግለሰቦችን ከፖለቲካው አውድ በማስወገድየእድሜ ልክ ገዢ የመሆን ሕልም ውስጥ ወድቋል፡፡
ፓርቲያችን አንድነትም ለሀገራችን የሚጠቅመው ይህ ያለመቻቻልና የጥፋት ጎዳና ሳይሆን የመነጋገር፤ እንዲሁም አሸናፊ የሆነው ሃሳብ ተቀባይነት እንዲያኝና የዜጎች መብት ለስልጣን ሲባል ሳይሸራረፍ እንዲከበር በሠላማዊ ትግል አቅጣጫ መግፋት ተገቢ መሆኑን በጽናት ያምናል፡፡ የአመራር አባሎቻችንም ሳይገድሉ እየሞቱ፤ ሳይደበድቡ እየተደበደቡ፤ ሳያስሩ እያታሰሩ ለህዝቡ የሚገባው ነገር እንዲደረግ ያለመታከት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
አንድነት ህጋዊ መስመር በመከተልና በጠበበው የፖለቲካ ምህዳር ውስጥም ቢሆን ዓላማውንና ግቡን ፍፁም ሠላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ ለህዝቡ ማድረስ የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ እንዳለም ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ በህዝቡ ዘንድ ያለው ተቀባይነትም እጅግ ጨምሯል፡፡ ነገር ግን ተቀባይነታችን በጨመረ ቁጥር በስጋት ባህር የሚዋኘው ገዢ ፓርቲ በአመራሮቻችንና አባሎቻችን ላይ እየፈፀመ ያለው ግልጽ በደልና በማናለብኝነት በጠራራ ፀሐይ ለመደብደብ የሞራል ችግር በሌለባቸው የደህንነት ሠራተኞችና ሆድ አደር ግለሰቦችን በማሰማራት እየተፈፀመ ያለው ግፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ቀጥሏል፡፡
ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራር የሆኑት የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ስዩም በጠራራ ፀሀይ ታፍነው እንቅስቃሴያቸውን የማያቆሙ ከሆነ እንደሚገደሉ የተነገራቸው ሲሆን፤ የአዲስ አበባ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በጠራራ ፀሐይ ወደቤታቸው ሲገቡ ከኋላቸው በድንጋይ ተመትተው ሲወድቁ ሞቱ ብለው ጥለዋቸው ሄደዋል፡፡ እንዲሁም የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የመሀል ቀጠና አደራጅ አቶ ደረጀ ጣሰውን የማይታወቁ ግለሰቦች እንፈልግሀለን በማለት በመኪና አፍነው ለመውሰድ ትግል ሲያደርጉ ባሰሙት ጩኸት ህዝቡ ያስጣላቸው ቢሆንም አይናቸውን በቦክስ በመመታታቸው በከፍተኛ ህክምና ሊተርፉ ችለዋል፡፡ አንድነት ላይ እየተፈፀመ ያለው የአደባባይ አፈና በዚህ የሚያበቃ አይደለም፡፡ በቅርቡ አንድነትን የተቀላቀሉት አቶ አስራት አብረሃምም በኦሮሚያ ፖሊሲ ታፍነው እስካሁን ያሉበት አይታወቅም፡፡ ይህ በአዲስ አበባ አመራሮች የተፈፀመ ሲሆን ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ አባሎቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለውን አፈናና እስራት ለመዘርዘር ከባድ ነው፡፡ ለአብነትም በወላይታ ሰዶ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር በሆኑት የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ እና ምክትል ኃላፊው አቶ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም የዞኑ የምክር ቤት አባላት፣ በደሴ ከተማም በተመሳሳይ ሁኔታ በአቶ አዕምሮ አወቀ ላይ የተፈፀመው ውንብድና፣ ድብደባ እስራትና አፈና ጠቋሚ ማስረጃዎች ናቸው፡፡
በአመራሮችና አባላት ላይ ከሚፈፀመው አፈናና ክትትል በተጨማሪ የፓርቲውን ስም ለማጥፋትና ተቀባይነት ለማሳጣት አይጋ-ፎረምን የመሳሰሉ የሥርዓቱ ቀላጤ ሚዲያዎች ፀረ-ሠላም ከሚሏቸው ኃይሎችና አሸባሪ ብለው ከፈረጁአቸው አካላት ጋር ግንኙነት እንዳለን የሚያስመስል የልቦለድ ዘመቻ ከፍተዋል፡፡ ይሄ ሁሉ የሚያሳየው ፓርቲያችን ጠንክሮ መውጣቱን ሲሆን ከዚህ በኋላ በአፈና፣ በድብደባና በእስር እንዲሁም በፍረጃ አንድነትን ወደ ኋላ መመለስ እንደማይችል ለማረጋገጥም እንወዳለን፡፡
ይልቁንም ገዢው ፓርቲ ካለፈው ስህተቱ በመማር፣ ከስለላ፣ ከፍረጃና ከአፈና በመላቀቅ ወደ ውይይት እንዲምጣ አሁንም ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በአፈናና በጉልበት አሁንም ቀጣዩን ምርጫ ለመቀልበስ መሯሯጥ ባለዕዳ የሚያደርገው ገዢውን አካል መሆኑን ለማስገንዘብም እንወዳለን፡፡
የ23ት አመቱ የግንቦት 2ዐ ፍሬ ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ቢኖር ይህ አስከፊ ስርዓት ያነበረው ጭቆናና በደል እስር እንግልትና በተጽእኖ ከሀገር መሰደድ ከሦስት ሺ ዓመታት በላይ የተገነባው አብሮነት አደጋ ላይ መውደቁ ተጠቃሽ ሊሆን ይችላል፡፡ የነፃነት ቀን ነው በሚሉት በግንቦት 2ዐ ዋዜማ እንኳ የዞን 9 ጦማሪዎች በማእከላዊ መከራ እየተቀበሉ ሲሆን የእስር እርምጃው ቀጥሎ ደራሲ አስራት አብርሃም ታፍኖ ከመሰወሩ ባሻገር የዕንቁ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በተጨማሪ ወደ እስር ተግዟል፡፡ ይህም የግንቦት 2ዐ ፍሬ መሆኑ ነው፡፡
ምን አልባትም ሥርዓቱ የምርጫ 97 ሽንፈትን ተከትሎ በግብታዊነት ወደ መሰረተ ልማት ማስፋፋት በማተኮር አንዳንድ ቁሳዊ ልማት ለማሳየት ቢጣደፍም ማህበራዊ ልማትን ቀብሮ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብትን እረግጦ፤ ልማት አስመዝግቤአለሁ እያሉ አገዛዝን በኃይል ለማስቀጠል መሞከር የከፋ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል መገንዘብ ይገባል፡፡
በመጨረሻም ፓርቲያችን ዛሬም የዚችን ሀገር ዘርፈ ብዙ ችግር በኃይል ለማዳፈን ከመሞከር ወደ ውይይት እና ብሔራዊ መግባባት ማዘንበል ጠቃሚ መሆኑን አበክሮ ይገልፃል፡፡
ድል የሕዝብ ነው!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ግንቦት 19 ቀን 2ዐዐ6 ዓም
አዲስ አበባ
አዲስ አበባ

ልማታዊ ፓትርያርክ (ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ)

                        May 29, 2014

              ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
          nigatuasteraye@gmail.com
         ግንቦት ፳፻፮ ዓ.ም.
መግቢያይህችን ክታብ በዚህ ርእስ እንዳዘጋጅ ያነሳሳችኝ “ልማታዊ መንግስት-እንደ ቻይና፤ ነገሩስ ባልከፋ” በሚል ርእስ ዶ/ር ደስታው አንዳርጌ ግንቦት ፲ ቀን ፪ሺ፮ ዓ.ም ያቀረቡልን ክታብ ናት። [ሙሉውን እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ:: ] ከ’ሀ’ እስከ ‘ሠ’ ተዘርዝራ የቀረበችውን ይህችን ክታብ ሳነብ፤ እንደኔ ያለውን እንቅልፋም ተማሪ ቀስቃሽ ምሁር፤ በክታባቸው አማካይነት ጣቴን ይዘው ወደ ጠቀሷቸው አገሮች ወደ እስያ፤ ቻይና፤ ታይዋንና ጃፓን በመንፈስ ወሰዱኝ።
ተመልከት! ልማታዊ መንግስት ይሉሀል:: ሰላም በምድራቸው፤ በጎ ፈቃድ በዜጎቻቸው አዕምሮ እና ስነ ልቡና ላይ ልማትን የመሰረቱ እነዚህ የቻይና የጃፓንና የታይዋን መንግስታት ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት የዘረጋው የልማት ግን፤ በጅብና በአህያ፤ በተኩላና በበግ፤ በጃርትና በዱባ መካከል የተዘረጋ የልማት ተቃራኒ ጥፋት ነው።” እያሉ በማነጻጸር ያስጎበኙኝ መሰለኝ።

የወያኔ ጥላቻ ፍሬ

 
                                        ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም 
 ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ 
የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና 
በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ 
ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-
ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው 
የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር 
ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ 
ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ 
አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ 
ነው፤‹‹የለሁበትም!›› እያለ ነው። 
 የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው፤ የሚለምነው ትግሬ ለብዙ 
ሰዎች ትግሬና ወያኔ አንድ መስሎ እንደሚታየው ያውቃል፤ አብዛኛው ሰው በወያኔ ላይ ያለውን ስሜት 
ያውቃል፤ ስለዚህም ሲለምን ሰዎች በወያኔ ላይ ያላቸውን ስሜት ስለሚያራግፉበት እየተሸማቀቀ ነው፤ 
አንድ የትግራይ ቄስ ከአርሲ ነኝ አሉኝና ለምን እውነቱን አይናገሩም ስላቸው እውነቱን ስናገር የማገኘው 
ስድብ ብቻ ነው አሉኝ፤ እኒህ ሰው ምን በወጣቸው የወያኔን ኃጢአት ተሸካሚ ይሆናሉ፤ በሌላ በኩል 
ደግሞ በትግሬነቱ የተጠቀመ አለ፤ እኔ የማውቀው የደርግ ወታደር የነበረ ትግሬ ቆስሎ ከውትድርና ወጣና 
በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የጥበቃ ሥራ ላይ ነበር፤ በጣም ይቸግረው ነበር፤ ሚስቱ ሕመምተኛ 
ነበረች፤ የቤት ኪራይ መክፈል ይቸገር ነበር፤ ዛሬ ግን የሚለብሰው ልብስ ሌላ ነው፤ ከኑሮውም ተርፎ 
ለሲጃራና ለጫት እያወጣ ነው፤ ወይም ሌሎች እያወጡለት ነው፤ ትግሬነታቸው ብቻ እንዲህ የደላቸው 
በጣም፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህም በወያኔ አገዛዝ ትግሬ ሁሉ ተጠቅሞአል ማለት ከጉልሁ እውነት 
ጋር የሚጋጭ ስሕተት ነው፤ አብርሃ ሰዎች ትግሬ ሁሉ ተጠቃሚ ሆኗል ሲሉ ‹‹ያመኛል›› ማለቱ ይገባኛል። 
 ወያኔ ትግሬ በመሆኑ ብቻ ትግሬ ሁሉ ዕዳ አለበት ማለት እንደወያኔ ማሰብ ነው፤ ወንጀል በዘር 
አይተላለፍም፤ እያንዳንዱ ሰው ለሠራው ሥራ ሁሉ ኃላፊነትን ይወስዳል፤ ጊዜው ሲደርስ ውጤቱንም 
ለመቀበል ይገደዳል፤ ይህ የሚሆነው ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ ኃይል በጎ መንፈስ አድሮበት፣ አእምሮው 
በትምህርት ተገርቶ በትክክል ማሰብ ሲችል ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን በአለበት ሁኔታ በጎ መንፈስ 
የራቀው ይመስላል፤ አእምሮም ጭራሹኑ በእኩይ መንፈስና በጥላቻ እየዛገ ነው፤ ስለዚህ ያስፈራል፤ 
በደቡብ ሱዳን ሁለት መቶ ሰዎች በዘር ተለይተው ታረዱ ሲባል ያስፈራል፤ በናይጂርያ፣ በኮንጎ 
የሚካሄደውን የዘርና የሃይማኖት እልቂት ስንሰማ ያስፈራል፤ በ1997 ዓ.ም. መለስ ዜናዊና አዲሱ ለገሰ 
እንዳስታወሱን የሩዋንዳ የጎሣ እልቂት በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ አለ፤ የቅርብ ተኳሽ የሆነው የአግዓዚ 
ጦርም አድፍጦ መጠበቅ ያስፈራል፤ ሌላውም ይህንን አውቆ አድፍጦ መጠበቁ ያስፈራል፤ ሰማይ ጠቀስ 
የሠሩት፣ የሥልጣን ኃላፊነትን ችላ ብለው በሥልጣን የሚነግዱና የሚከብሩት፣ የማይኖሩበትን ሕንጻ 
የሚክቡት፣ ከሕዝብ ጋር ያላቸው የአይጥና የድመት ኑሮ ያስፈራል፤ አቶ አስገደ ወያኔ መደንገጡን 
ነገረ ኢትዮጵያ
ግንቦት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 14 2
ርዕሰ አንቀፅ
 እንዲህም ተብሏል!
ነገረ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ ጥር 2006
ዓ.ም ተመሰረተች፡፡ ነገረ-ኢትዮጵያ
በሰማያዊ ፓርቲ አሳታሚነት
የምትታተም ፖለቲካዊ፣ ወቅታዊ፣
ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን
የምትዳስስ በየሳምንቱ አርብ
የምትወጣ ጋዜጣ ናት፡፡
ጋዜጣዋ ሚዛናዊና ነጻ ሆና የማገልገል
መርህ አላት፤ ማንኛውም ሀሳብ በነጻነት
የሚስተናገድባትና የሚንሸራሸርባት
እንድትሆን እንፈልጋለን፡፡ ገዥው
ፓርቲም ቢሆን አቋሙንና ፖሊሲውን
ለመግለጽ ቢፈልግ የሰፊ ሚዲያ ባለቤት
ነው ብለን ዕድሉን አንነፍገውም፤
በራችን ለሁሉም ክፍት ነው፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያ
የአሳታሚ አድራሻ:-
የካ ክ/ከተማ ቀበሌ 09/10 ቤት ቁ.460
E-mail: info@semayawiparty.org
P.O.Box: 180298
ዋና አዘጋጅ ፡- ጌታቸው ሺፈራው
የካ ክ/ከተማ ቀበሌ 01/02
ቤት ቁ. 07/859/14
E-mail:getcholink@gmail.com
ስልክ ቁጥር: 09-10-45-99-32
ምክትል ዋና አዘጋጅ፡- በላይ ማናዬ
የካ ክ/ከተማ ቀበሌ 01/02 ቤት
ቁ.099
E-mail: belaymb@gmail.com
ስልክ ቁጥር: 09-20-19-09-72
አምደኞች ፡-
ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም
ታዴዎስ ታንቱ
ታምራት ታረቀኝ
አፈወርቅ በደዊ
እያስፔድ ተስፋዬ
ሕትመትና ክትትል
 ሳሙኤል አበበ
0913 98 46 40
አታሚ፡- ሰማያዊ ፓርቲ
ሌይ አውት ዲዛይን ፡-
 ደሳለው ጌትነት
ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ዓለም በቴክኖሎጅና በኢ
ኮኖሚው በእጅጉ የተለወጠበት፣ ለሰብአዊ መብትና ዴሞ
ክራሲ መከበር በር የተከፈተበት፣ በሉላዊነት ምክንያት
የዓለም ህዝቦች ከመቼውም ጊዜ በላይ የተሳሰሩበትና ለመ
ተሳሰርም እድል የተገኘበት ጊዜ ነው፡፡ ይህን ነጻነታቸውን
ካገኙ 20 አመት ያልበለጣቸው አገራትም ነጻነታቸውን በአ
ግባቡ ተጠቅመውበት ህዝባቸውን ለመቀየር ችለዋል፡፡ ለአ
ብነት ያህልም ደቡብ አፍሪካን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ከደቡብ
አፍሪካ በተጨማሪ እ.ኤ.አ በ1991 የራሷን አስተዳደር የመ
ሰረተችውና ዓለም እውቅና ያልሰጣት ሶማሊ ላንድ እንኳ
በፍትሃዊ ምርጫ፣ በሰላም መሪዎቿን በመምረጥ በአፍሪካ
ቀንድ ብቸኛዋና በዓለም መንግስታት በአገርነት እውቅና ላገ
ኙትም በምሳሌነት እየተጠቀሰች ትገኛለች፡፡
በሌላ በኩል አገራችን ኢትዮጵያ ረዥም የነጻነትነት
እድሜ ያላት ብትሆንም አሁን ላይ ቀደም ብላ ከቅኝ አገ
ዛዝና ጭቆና ነጻ እንዲወጡ ካገዘቻቸው የአፍሪካ አገራት
ባነሰ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች፡፡ ለዚህ ኋላ ቀርነቷ ደግሞ
ባለፉት 23 አመታት ያገኘቻቸውን አጋጣሚዎች ገዥዎቹ
መጠቀም ባለመቻላቸው እንደዋነኛ ምክንያት የሚጠቀሱ
ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት ስልጣን ላይ የሚገኘው ህወሓት/
ኢህአዴግ መጀመሪያ ላይ የዓለምን ማህበረሰብ ቀልም
ለመሳብ መሰረታዊ ለውጦችን አድርጎ የነበርና እነዚህንም
በህገ መንግስቱ ላይ ያስቀመጠ ቢሆንም ሲተገብራቸው
ግን አልታየም፡፡ በተለይ ስልጣን ከያዘ ከአራትና አምስት
አመት በኋላ ወደ ነበረበት ‹‹ግራ ዘመምነት›› በመመለስ
በህገ መንግስቱ የፈቀዳቸውን መብቶች እንደገና በግልጽ
ሲደፈጥጥ ተስተውሏል፡፡
ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን እንደያዘ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ
የህትመት ሚዲያዎች ፈቃድ አግኝተው ለህዝብ መረጃ
በማድረስ ላይ የነበሩ ቢሆንም ሚዲያ ህዝብን ማንቃቱን
ያልወደደው ገዥው ፓርቲ እየቆየ አፈናውን ተያይዞታል፡፡
በመሆኑም በርካታ ሚዲያዎች ወደ አደባባዩ ወጥተው እን
ደገና ለመዘጋት ተዳርገዋል፡፡ ጋዜጠኞች ታስረዋል፤ እየታ
ሰሩም ነው፡፡ በጫናው ምክንያት ተሰደዋል፤ እየተሰደዱም
ይገኛሉ፡፡ በተለይ ህወሓት/ኢህአዴግ የደነገጠበት የ1997
ምርጫን ተከትሎ በርካታ የህትመት ሚዲያዎች ሲዘጉ፣
ጋዜጠኞች በአገር ክህደት ወንጀል ተከሰው ዘብጥያ ወርደ
ዋል፡፡ በርካቶቹ ተሰደዋል፡፡ ይህን ሁሉ ጫና ችለው ለህ
ዝባቸው መረጃ ለማድረስ የጣሩት እንደ እስክንድር ነጋ፣
ርዕዮት ዓለሙና ውብሸት ታየ ያሉት ደግሞ በአሁኑ
ወቅት ‹‹አሸባሪ›› ተብለው እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
በቅርቡ ከዞን ዘጠኝ አባላት ጋር የታሰሩት ሶስት ጋዜጠኞች
ስርዓቱ ባለፈው 23 አመት ያደበረውን የአፈና ባህል አጠ
ናክሮ እንደቀጠለ የሚያሳይ ሆኗል፡፡
በተመሳሳይ የመደራጀት፣ የመሰብሰብና ሌሎች መብቶች
ባለፈው 23 አመት ህገ መንግስቱ ላይ ከሰፈረው በተቃራኒ
እየተደፈጠጡ ቀጥለዋል፡፡ በአንድ ወቅት ጠንካራ ተቃዋሚ
እንዳጣ በግልጽ ሲናገር የነበረው ገዥው ፓርቲ ከ1997
በኋላ ለተቃዋሚዎች መፈናፈኛ ላለመስጠት በርካታ ፀረ
ህገ መንግስታዊና አፋኝ አዋጆችን አጽድቆ በህግ መሳሪያ
ነት እየገዛ ቀጥሏል፡፡ ባለፉት 8 አመታት ህገ መንግስቱ የፈ
ቀደው ሰላማዊ ሰልፍ በገዥው ፓርቲ ተከልክሎ ቆይቷል፡
፡ በአሁኑ ወቅትም በተቃዋሚዎች ግፊት የተጀመሩ የተቃ
ውሞ ሰልፎች በገዥው ፓርቲ የደህንነትና የፖሊስ ኃይል
የሚጠበቅባቸውን ያህል ሚና እንዳይወጡ ተከልክለዋል፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎች ህጋዊ በሆነ መንገድ የስብሰባ አዳራ
ሽና ሌሎቹንም ለትግሉ ሊያገኙዋቸው የሚገቡ አገልግሎ
ቶችን እንዳያገኙ ገዥው ፓርቲ ጠንክሮ እየሰራ ይገኛል፡፡
ይህም የፖለቲካ ኃይሎች በሰላማዊ ትግሉ ተስፋ እንዲቆ
ርጡና ሌሎች ሰላማዊ ያልሆኑ አማራጮችን እንዲከተሉ
እስከማድረግ ደርሷል፡፡ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በተጨማሪ
ሲቪክ ማህበራትና ሌሎችም ለህዝብ ጥቅም የሚቆሙ የህ
ዝብና የመንግስትን ተቋማት አንድም ለራሱ መጠቀሚያ
ማድረጉ ከዚህም በተጨማሪ ስራቸውን እንዳይተገብሩ መሰ
ናክል መፍጠሩ ህዝብ ድምጹን የሚያሰማበት መድረክ እን
ዲያጣ ተደርጓል፡፡
ሚዲያ፣ ተቃዋሚዎችና ተቋማት በመዳከማቸው ገዥው
ፓርቲና ፖለቲከኞቹ ያለምንም ተጠያቂነት የአገሪቱን
ሀብት ተጠቅመውበታል፡፡ በመሆኑም ባለፉት 23 አመታት
ከአገርና ከህዝብ ጥቅም ይልቅ ግለሰባዊ፣ የፓርቲና ቤተሰ
ባዊ ጥቅምን ማጋበስ የስርዓቱ ባህሪ እንደሆነ ታይቷል፡፡
በዚህም ምክንያት ህዝብ ከአገሩ ኢኮኖሚ የሚገባውን እን
ዳያገኝ ተደርጓል፡፡ በሙስና፣ በስርዓቱ ደጋፊነትና በመሳሰ
ሉት ካልሆነ ህጋዊ መንገድን የያዘ ዜጋ ስራ መስራት ባለ
መቻሉ አገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እን
ዳታገኝ ተደርጋለች፡፡ ምሩቃን፣ ከስርዓቱ ጋር ግንኙነት የሌ
ላቸው ምሁራንና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ህጋዊ
በሆነው መንገድ ጥቅም ባለማግኘታቸው ለስደት፣ ለድህ
ነት ተዳርገዋል፡፡
በተቃራኒው ግን ይህ ያፈጠጠ እውነታ ተገልብጦ የግንቦት
20 ፍሬዎች እየተባለ ህዝብ ባዶ ፕሮፖጋንዳ ይጋታል፡
፡ በመሆኑም ገዥው ፓርቲ እንደሚለው ግንቦት 20 የኢ
ትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱን ያገኘበት ሳይሆን ከአንዱ አምባገነን
ስርዓት ወደ ሌላ መልኩን የቀየረ አምባገነን ስርዓት የተሸ
ጋገርንበት መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ እናም ያለን
በትን ትክክለኛ መልክ ሸፋፍኖ ስለሌለ ለውጥ ህዝብን በፕ
ሮፖጋንዳ ከማደንቆር ይልቅ ወደ ትክክለኛ የህዝብ ተጠቃ
ሚነትና ነጻነት የሚያደርሰውን መንገድ ይዞ ለአዲስ ለውጥ
መስራት እንደሚገባ መገንዘብ ይገባል

Friday, 23 May 2014

EHSNA Condemns Human Rights Violations in Ethiopia

May 19, 2014

Washington, D.C. – The Ethiopian Heritage Society in North America (EHSNA) condemns the killing of students in Oromia region in Ethiopia. Furthermore, EHSNA condemns the arrests, torture, and imprisonment of Ethiopians through out Ethiopia and calls on all human rights organizations to put pressure on TPLF/EPRDF regime for its heinous crimes.Ethiopian Heritage Society in North America (EHSNA)
For the past month and a half, the situation in Ethiopia has been very disconcerting. The vast ongoing human rights violation by the TPLF government has urged the Ethiopian Heritage Society In North America (EHSNA) to speak and condemn the ongoing onslaught on Ethiopian citizens. The level of instability in the country has never been more apparent than ever before.
Oromo students have been peacefully protesting against aland policy where the government intends to implement. Largely, the protests took place in universities in towns such as Ambo, Jimma, Wellega and so on. According to BBC, in Ambo, 125km (80 miles) west of Addis Ababa, eye witnesses reported at least 47 students were killed by security forces during the days preceding May 2, 2014.
Instead of addressing the issue peacefully the TPLF/EPRDF regime security forces used live ammunition at unarmed student protestors killing and leaving several hundred causalities in various parts of Oromia region.
According to human rights watch the TPLF government is, “showing increasing intolerance of any criticism of the government and further restrictions on the rights to freedom of expression and association.” Hundreds of students and perhaps in the thousands now have been so far imprisoned and expelled in relations with the protests.
The regime has been systematically implementing an ethnic cleansing of Amharas. As a result thousands of Amharas have been expelled by and still continue to be ethnic cleansed from South as part of the government’s land policy. In reality, the land policy is a façade to extend its systematic implementation of confiscating land from poor villagers. The regime systematically incites violence between ethnic groups to create mistrust and hate among them. . Such an agenda has been advantageous for extremists group to exploit the policy and in turn carry out violence. This agenda disguised as policy is eroding the communal relationship and harmony that has existed for centuries
The imprisonment and intimidations of bloggers and journalists is another case that has been increasingly unsettling. Several Ethiopian journalists languish in prisons for merely expressing their opinions. Just recently, the TPLF regime arrested young bloggers, also known as zone9 bloggers, for blogging about societal issues affecting the country. The zone9 bloggers were jailed without due process and effectively sent to prison where they still remain in horrendous conditions. They have been denied access to their families and lawyers and are being imprisoned in Makelawi federal prison which is infamous for torturing prisoners. According to the Committee for protecting Journalists (CPJ), “Ethiopian authorities are turning the peaceful exercise of free expression into a crime.”
The Oromo students, as any other group of students, have the right to peacefully protest and be herd, Amharas have the right to live where they wish, and Journalists and bloggers have the right to free speech without any form of repression and intimidation. The EHSNA does not advocate any form extremists’ ideologies or align itself with any political groups; however, the question of human rights is a universal obligation where every citizen and organization must stand guard diligently. As a society based in democratic country, we support and believe in these basic human rights ideals.
The government’s gross human rights violation and divisive character has put into question the very fabric of Ethiopian identity and the future prospect of the country. Preserving and promoting Ethiopia’s heritage is only possible when the rights of its people are respected and the essence of Ethiopia stands firm. Thus, EHSNA condemns the killings, arrests, torture, and imprisonments and calls on all human rights organizations to put pressure on and condemn the TPLF government for its heinous crimes.
For more information, email: pr@ehsna.org

A Democratic Hero who deserves our appreciation!

May 23, 2014

by Nesanet Nerese
For a successful revolution it is not enough that there is discontent. What is required is a profound and thorough conviction of the justice, necessity and importance of political and social rights. B. R. Ambedkar (Roughly translated in to Amharic: ወጤታማ የሆነ ፖለቲካዊ ለወጥ ‘ኣብዮት’ ለማመጣት የሚያሰፈልገዎ በሆኔታዎች መጥፎ መሆን ማላዘን አይደለም ይልቁንስ ዋናው አስፈለጊው ነገር ለፍትህ ለፖለቲካዊ እና ማህበረስባዊ መብት መከበር ኣስፈላጊነት ጠንካራ የሆነ እምነት ይዞ ማራመድ እንጂ)Abebe Gellaw Ethiopian Democratic Hero
Yes, this Quote from Ambedkar speaks a volume about the need of having a strong belief (conviction) in change i.e. for a real change to take place in a society where there is a deep rooted discontent because of injustice.
So in this respect it is fair to say t