ኢህአዴግ ጣና በለስን ለምን አፈራረሰው? “በሩ ይከፈት፣ በአባይ ጉዳይ አገራዊ አቋም እንያዝ”
Negash | June 7th, 2013“ጣና በለስን አፈራርሶ ያስዘረፈ ፓርቲና አመራሮቹ አሁን አባይን ለመገደብ የተነሱበት መነሻ ለአብዛኛው የኢህአዴግ አባላት እንቆቅልሽ ነው”
By Goolgule.comJune 7, 2013

በግብጽ ረዳትነት፣ በሱዳን መሪነት መንግስት ለመሆን የበቃው ህወሃት/ኢህአዴግ ግዙፉን የጣና በለስ ፕሮጀክትና ንብረቱ
እንዲዘረፍ ያደረገበትን ምክንያት በማንሳት መከራከር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ። የግብጽ ፕሬዚዳንት ሙርሲ እንዳደረጉት በአገር
ጉዳይ ሁሉንም ያሳተፈ ግልጽ አቋም እንዲያዝና አጋጣሚውን በመጠቀም ብሔራዊ ህብረት እንዲፈጠር ኢህአዴግ በሩን ሊከፍት
እንደሚገባ ተገለጸ።