እንደሚታወቀው ኢህአዴግ የሚባለው ገዢ ቡድን መንበረ ስልጣኑ ላይ ከወጣ
ጀምሮ ብዙ አሳዛኝ ነገሮችን በህዝባችን እና በሀገራችን ላይ ሲፈፅም ቆይቷል አሁንም እየፈፀመ ይገኛል። ከነዚህ
አሳዛኝ ነገሮች አንዱ እንደ አንድ ሀገር በአንድነት ለዘመናት ብዙ ርቀት የተጓዘን ህዝብ ወደ ኋላ በመመለስ የዘር
እና ጎሳ ልዩነትን በሚያጎላ አካሄድ፤ ቋንቋን እና ዘርን መሰረት ያደረገ የከሸፈ የፌድራሊዝም አወቃቀር ስርዓት
በመከተል እንደ ሀገር ብሄራዊ ስሜት እንዳይኖረን የክልል መንግስት የሚባል መዋቅር መፈጠሩ ነው።
ሲመስለኝ ፌድራሊዝም በራሱ አስፈላጊ የሚሆነው እንደ ሀገር ተበታትነው በተለያየ አገዛዝ የነበሩ አካባቢወች
ልዩነታቸውን በማቻቻል ወደ አንድነት መንግስት ለመምጣት ሲያስቡ እንደ መሸጋገሪያ ራስገዝ የሆነ የፌድራል ስርዓት
ይመሰርታሉ፤ እነዚህን ራስ ገዝ ክልሎችም በበላይነት የሚመራና የሚቆጣጠር ከሁሉም አካባቢ የሚወከሉ አካላትን ያካተተ
ማዕከላዊ መንግስት ይመሰረታል።
Friday, 29 March 2013
Tuesday, 26 March 2013
የኢትዮጵያ መንግስት እስክንድር ነጋ የታሰረው በአሸባሪነቱ እንጅ በጋዜጠኝነቱ አይደለም ሲል ለአውሮፓ ህብረት መልስ ሰጠ
ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ አገዛዝ በእስር ላይ የሚገኘውን እውቁን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በተመለከተ ከአውሮፓ
ህብረት የፓርላማ አባላት ለቀረበት ጥያቄ በጽሁፍ በሰጠው መልስ ” እስክንድር ነጋ የጋዜጠኛነት ስራውን በመስራቱ
ሳይሆን አሸባሪ ድርጅቶችን ሲረዳ በመገኘቱ ነው” የተፈረደበት ብሎአል።
እስክንድር ነጋ በህቡእ ከሚንቀሳቀሰው ግንቦት7 ከተባለው ድርጅት ጋር ግንኙነት እንደነበረው፣ ከኤርትራ ወደ
ኢትዮጵያ እየሰረጉ ለሚገቡ አሸባሪዎች ስልጠና ይሰጥ እንደነበርና ከኤርትራና ከግንቦት7 መሪዎችንም በስውር ያገኛቸው
እንደነበር” ገልጿል።
Subscribe to:
Posts (Atom)